ሥራ ከቶ ሳይሠሩ: በሰው ነገር እየገቡ: ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና.
እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን.
እናንተ ግን: ወንድሞች ሆይ. መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ
በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር: ይህን ተመልከቱት. ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ
ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት. [2 ወደ ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕራፍ 3 11-15
Tłumaczony, proszę czekać..
